Fana: At a Speed of Life!

ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸነፈ

ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ18ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ የነገሌ አርሲን የማሸነፊያ ግቦች ከቤ ብዙነህ እና ዳዊት ተፈራ (በፍጹም ቅጣት ምት) አስቆጥረዋል።

በዕለቱ በተደረጉ የሊጉ 18ኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች መቐለ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ ቡና 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ሲለያዩ፤ አርባምንጭ ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1፣ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.