Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ባለቤት ለማድረግ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የሚያስችል የውል ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አሥተዳደር ቢሮ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ናቸው፡፡

በዚሁ መሠረትም ስምምነቱ መምህራንን ጨምሮ በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ስምምነቱ በአነስተኛ የወለድ መጠን በ25/75 የብድር መርሐ ግብር የሚከናወን ነው ተብሏል፡፡

ቀደም ሲል ተደራጅተው በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ቤት ፈላጊ መምህራን በመርሐ ግብሩ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በከተማ አሥተዳደሩ ለሚገኙ ቤት ፈላጊ ሠራተኞች በዝቅተኛ የወለድ መጠንና በ20 ዓመት የሚከፈል ብድር ማመቻቸቱን አስታውቋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ ከ40 ሺህ በላይ የመንግሥት ሠራተኞችን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱም ነው የተገለጸው፡፡

በጀማል አህመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.