Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወባ በሽታን ለመከላከል እየተሰራ ነው 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተጋላጭ አካባቢዎችን በመለየት የወባ በሽታን የመከላከል እየተሰራ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የወባ መከላከል ፕሮግራም ከፍተኛ ባለሞያ ዘሪሁን ደሳለኝ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት፤ የወባ በሽታን መከላከ እና መቆጣጠር በዘርፉ ዋና ትኩረት ከተሰጣቸው መካከል አንዱ ነው።

በክልል ካለው 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ለወባ ተጋላጭ በመሆኑ የመከላከል ሥራው ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ጠቁመዋል።

የበልግ ዝናብ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የወባ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ማህበረሰቡን ግንዛቤ እንዲኖረው እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች ውስጥ ወላይታ እና ጋሞ 66 በመቶ የወባ በሽታ ጫና እንዳለባቸው ጠቁመው፤ ማህበረሰቡን ያሳተፈ የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል ።

ጫና በሚበዛባቸው አካባቢዎች በየደረጃው በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመው፤ ከበልግ ዝናብ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የወባ በሽታ ለመከላከል ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ ክትትል እና ድጋፍ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

በቀጣይ የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ፣ የመኝታ አጎበር አቅርቦት እና አጠቃቀም ከፍ በማድረግ እና የማህበረሰብ ባለቤትነትን በመፍጠር  ጠንካራ ሥራዎች እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

በኢብራሂም ባዲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.