በክልሉ ወረርሽኝና ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ጫና በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወረርሽኝ እና ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ጫና በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል አለ የክልሉ ጤና ቢሮ።
የቢሮው የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት የግማሽ ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ በሀላባ ቁሊቶ አካሂዷል፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በወቅቱ እንዳሉት፥ ለወረርሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓት በመገንባት ጠንካራ የቅኝትና ምላሽ ስራዎች ተሰርተዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት የወረርሽኞችን አሰሳና ቅኝትን ለማጠናከር፣ የማህበረሰብን ግንዛቤ ይበልጥ ለማሻሻልና ከአጎራባች ክልሎች ጋር በቅንጅት መሰራቱን ጠቅሰው፥ በወባ፣ ኩፍኝ እና ኮሌራ በሽታ የነበረውን ጫና በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል።
የጤና አገልግሎቶችን በምርምርና ቴክኖሎጂ ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተፈጸሙ መሆኑን ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።