‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል የረጅም ዘመን እድሜ ያለውን ትስስር ለማጠናከር ሮም በመሄድ በጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
መሪዎቹ በመተግበር ላይ ያለውን የትብብር አፈፃፀም በመገምገም በባለብዙ ወገን እንዲሁም አዳዲስ የትብብር መስኮችን በተሻሻለ የኢንቬስትመንት መጠን ለመከወን የሚቻልባቸውን ጉዳይች ላይ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ የጣሊያን መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ትብብሮችን ለማጠናከር ሰርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር በጥቅምት 2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ወደ ኃላፊነት በመጡ በአጭር ጊዜ በሮም በመገኘት በምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የሰላም እና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ረገድ ጣልያን ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ አስመልክቶ ውይይት ተደርጎ ነበር።
ከዚህ ውይይት በኋላ መሪዎቹ ጠንካራ የስራ ግንኙነት የመሠረቱ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ በ2016 ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። ቀጣይ ውይይቶችም በጣሊያን እንዲሁም ሌላ ሀገራት ላይ በተካሄዱ ባለብዙ ወገን መድረኮች ተካሂዷል።
ጣሊያን የኢትዮጵያ ልማት ቁልፍ አጋር ናት። በኢንደስትሪ ብሎም እንደ ጤና፣ ግብርና እና ባሕላዊ ቅርስ ጥበቃ የረጅም ዘመን ደጋፊም ናት። የጣሊያን ኩባንያዎች እና የጣሊያን የልማት ትብብር ተቋም ሥራዎችን በንቃት እየደገፉ ይገኛሉ።
ሁለቱ መሪዎች በመጨረሻ ስብሰባቸው ለዘላቂ ልማት እና የተሻሻለ ኢንቬስትመንት ያላቸውን የጋራ ርዕይ አረጋግጠዋል።››
#PMOEthiopia