ኢትዮጵያ በ12ኛው የፓሪስ ፎረም ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በፈረንሳይ ፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 12ኛው የፓሪስ ፎረም ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡
ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በፎረሙ ላይ ባደረጉት ንግግግር ÷ ኢትዮጵያ በቡድን 20 ሀገራት ማዕቀፍ መሰረት ያላትን የእዳ ማሻሻያ እና አያያዝ ተሞክሮ አስረድተዋል፡፡
የአበዳሪ ሀገራት የእዳ ማሻሻያ ድርድር ሒደት አካታች፣ ገንቢ እና ትብብርን መሰረት ያደረገ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ሚኒስትር ዴዔታው አጋር አካላት በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ተሳትፎም አድናቆታቸውን ችረዋል፡፡
ተበዳሪ ሀገራት የዕዳ እፎይታን በወቅቱ ማግኘት እንዲችሉ ተገማችና ተጨባጭ የጊዜ ሰሌዳ ማበጀት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የአሰራር ሒደቶችን ለማዘመን እና የአከፋፈል መዘግየትን ለመቀነስ ደረጃውን የጠበቀ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረም አስፈላጊ መሆኑን ነው ያብራሩት፡፡
በአበዳሪና ተበዳሪ ሀገራት መካከል ያለውን መተማመንና ግልጽነት ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመው÷ በሒደቱ ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ሁሉም አካላት ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡
አሁን ላይ ኢትዮጵያ በቡድን 20 ሀገራት የጋራ ማዕቀፍ የእዳ ማሻሻያ እና እፎይታ ተጠቃሚ እንደሆነች መጥቀሳቸውንም ሚኒስትር ዴዔታው ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!