በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለአረንጓዴ አሻራ 276 ቦታዎች ተለይተዋል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 60 ሚሊየን በላይ ችግኖች ተዘጋጅተዋል አለ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ።
በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ደሳለኝ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቅቋል፡፡
ለመርሐ ግብሩ በክልሉ በሚገኙ 84 የችግኝ ጣቢያዎች 75 ሚሊየን ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት አሁን ላይ 60 ሚሊየን ያህል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለተከላ ዝግጁ መደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡
የተዘጋጁት ችግኞች የቡና፣ ደን፣ የእንስሳት መኖ እና ፍራፍሬን ጨምሮ ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው እጽዋት መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩል ለችግኝ ተከላ የሚሆኑ 176 ቦታዎች መለየታቸውን ጠቁመው÷ በአጠቃይ 1 ሺህ 354 ሄክታር መሬት ላይ ችግኝ እንደሚተከል ጠቅሰዋል፡፡
የቦታ ልየታው የሕዳሴ ግድብን ከደለል መከላከል የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ መሆኑን አቶ ፈቃዱ አስገንዝበዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ 234 ሺህ የማህበረሰብ ክፍሎች በቀጥታ እንደሚሳተፉ የገለጹት ዳይሬክተሩ÷ ሕዝቡ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለመርሐ ግብሩ ስኬታማነትም በየደረጃው የሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉም አስገንዝበዋል።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!