የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና እየወሰዱ የሚገኙት የ65 ዓመቷ እናት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል እየተሰጠ የሚገኘውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና እየወሰዱ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል የ65 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋዋ ወ/ሮ ታሪኳ አያሌው ይገኙበታል።
በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ የተወለዱት ወ/ሮ ታሪኳ ዕድሜ ሳይገድባቸው ተምረው ዛሬ ለ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተቀምጠዋል።
ጠንክሮ መስራት ከተቻለ ከፈለጉት ግብ መድረስ ይቻላል የሚሉት ወ/ሮ ታሪኳ፤ በአግባቡ ተምረው እና ዝግጅት አድርገው ፈተና እየወሰዱ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የልባቸውን መሻት ለማሳካት ዕድሜ እንደማይገድባቸውም ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል።
ትምህርትም በዕድሜ ሊገደብ እንደማይገባ በመናገር ሁሉም ሰው ባገኘው አጋጣሚ ትምህርት ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡
በትምህርት ቆይታቸው የአካባቢው ማህበረሰብ ጥረታቸውን በማድነቅ ሞራል ይሰጣቸው እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
በአብደላ አማን