Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ ውድድሮች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ትናንት ምሽት በስፔን ማድሪድ እና በቤልጂዬም ሂዩስደን በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡

በቤልጂዬም ሂዩስደን በተካሄደው የሴቶች 800 ሜትር ውድድር አትሌት ንግስት ጌታቸው 1 ደቂቃ 57 ሰከንድ 01 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት የራሷን ምርጥ ሰዓት በማሻሻል በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡

አትሌት ንግስት ባሳለፍነው ሳምንት በፈረንሳይ በተካሄደው የሴቶች 800 ሜትር 1 ደቂቃ 59 ሰከንድ ከ89 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ማሸነፏ ይታወሳል፡፡

በስፔን ማድሪድ በተደረገው የወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ደግሞ አትሌት አብዲሳ ፈይሳ 3 ደቂቃ 34 ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰኮንድ በሆነ ሰዓት በመግባት አሸንፏል፡፡

በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አትሌት ሞሲሳ ስዩም እና አትሌት ወገኔ አዲሱ 7ኛ እና 8ኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል፡፡

በተመሳሳይ በማድሪድ በተካሄደው የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር አትሌት ነፃነት ደስታ 3ኛ እንዲሁም አትሌት ትግስት ግርማ 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.