በኦሮሚያ ክልል ከ200 ቢሊየን ብር በላይ የሚያስመዘግቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ይስተናገዳሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት ዓመት ከ200 ቢሊየን ብር በላይ የሚያስመዘግቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ይስተናገዳሉ።
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሀይሉ አዱኛ የክልሉን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ ከኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 100 ሺህ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል ብለዋል።
ለዚህም በበጀት ዓመቱ ከ200 ቢሊየን ብር በላይ የሚያስመዘግቡ 10 ሺህ 500 ፕሮጀክቶችን ለማስተናገድ ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።
ከገቢ አንጻር ከጊዜ ወደ ጊዜ የክልሉ የገቢ አቅም ከፍ እያለ መምጣቱን ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ 283 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በተያዘው የመኸር ወቅት 11 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር እየለማ መሆኑን ጠቁመው፤ ከዚህም 368 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል ብለዋል።
በ2018 በጀት ዓመት የበጋ መስኖ ልማት ስራ 4 ሚሊየን መሬት በስንዴ ሰብል በመሸፈን 163 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት እንደሚሰራ አመልክተዋል።
በክልሉ በበጀት ዓመቱ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጠር እና 98 ሺህ ሄክታር መሬት ለመሸጫና ማምረቻ የሚቀርብ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በተጨማሪ 6 ሺህ 318 ሼዶች ለተጠቃሚዎች እንደሚተላለፉም አንስተዋል።
የትምህር ዘርፉን ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ያሉት ኃላፊው፤ በዚህም 2 ሺህ 353 የቡዑረ ቦሩ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 170 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና 22 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ ገልፀዋል።
በዚህም የክልሉን የተማሪ መጠን ወደ 13 ሚሊየን ለማሳደግ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።
በጤና ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት 127 ሞዴል መድኃኒት ቤቶችን ለመገንባት እና የጤና መድህን ተጠቃሚ ቁጥርን ወደ 31 ነጥብ 5 ሚሊየን ለማሳደግ ይሰራልም ነው ያሉት።
በክልሉ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ በሁሉም መስክ ጥረት እንደሚደረግ የቢሮው ኃላፊ አብራርተዋል።
በታምራት ደለሊ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!