Fana: At a Speed of Life!

ለቀጣዩ ትውልድ ምንዳ ለማውረስ ከተጀመሩ መርሐ ግብሮች መካከል አረንጓዴ ዐሻራ ዋናው ነው – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) መንግስት ለቀጣዩ ትውልድ ምንዳ ለማውረስ ከጀመራቸው መካከል አረንጓዴ ዐሻራ ዋናው ነው አሉ።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ መንግስት ለቀጣዩ ትውልድ ምንዳን ለማውረስ የሚተገብራቸው መርሐ ግብሮች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው።

ከመርሐ ግብሮቹ መካከል አንዱና ዋናው አረንጓዴ ዐሻራ መሆኑን ገልጸዋል።

ዜጎች የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ጥቅምን በመገንዘብ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሆነ በመጥቀስ፤ በዛሬው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብርም ህብረተሰቡ በከፍተኛ ደረጃ እየተሳተፈ ነው ብለዋል።

በመላ ሀገሪቱ ዜጎች እያደረጉ ላሉት ተሳትፎ አመስግነው÷ በቀጣይም ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.