Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በህዝብ ተሳትፎ ከ374 ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በህዝብ ተሳትፎ ከ374 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ‘ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ ፣ለላቀ የትምህርት ጥራትና ውጤት’ በሚል መሪ ቃል በወላይታ ሶዶ ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ የቢሮው ኃላፊ ፀሐይ ወራሳ እንዳሉት፤ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የውስጥ ግብዓትን ለማሟላት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተሰራው ስራ ውጤት አምጥቷል።

ህዝቡን በማስተባበር የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ 374 ሚሊየን 992 ሺህ 226 ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጸው፤ በተሰበሰበው ገንዘብ ት/ቤቶች፣ ተጨማሪ ብሎኮች ግንባታ፣ ጥገና እና ግብዓት የማሟላት ተግባር ተከናውኗል ብለዋል።

የትምህርት ዘርፍ ስራ ትውልድን የመቅረጽ፣ ብቃት ያለውን የሰው ሀይል የማፍራት፣ የሰውን ሀይል ምርታማነትን በማሳደግ ሀገር የመገንባት ተልዕኮ በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተመራ እና እየደተገፈው መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ ከተማሪዎች ምገባ አንጻር በዓለም ምግብ ፕሮግራም ሁሉንም የአርብቶ አደር ዞኖችን ጨምሮ በአምስት ዞኖችና 11 ወረዳዎች ተከናውኗል።

መንግስት ምግብ አጠር በሆኑ 14 ወረዳዎች አስቸኳይ ጊዜ ምገባ 73 ሺህ 833 ተማሪዎችን ተጠቃሚ በማድረጉ መጠነ ትምህርት ማቋረጥ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገልጿል።

በዮሴፍ ጩሩቆ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.