ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ከሚገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ልዑክ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያይቷል።
በተለያዩ መድረኮች በተካሄዱ ውይይቶች ስለኮሚሽኑ የእስካሁን የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም በትግራይ ክልል ምክክር በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ገለፃ ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ የተገኙ ኮሚሽነሮች በማንኛውም ሁኔታ መነጋገርና መመካከር እንደሚገባ ገልጸው÷ እንደ አንድ ሀገር ልጆች በመቀራረብ በትግራይም ሆነ እንደ ሀገር የገጠሙንን ችግሮች ለመፍታት መረባረብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ፓርቲዎቹ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱ እንዲጀመር አስቻይ ሁኔታ በመፍጠርና በንቃት በመሳተፍ ከኮሚሽኑ ጋር በቅርበት እንዲሰሩም በመድረኮቹ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የፓርቲ አመራሮቹ ኮሚሽኑ ፈታኝ ሁኔታዎችን በመቋቋም በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱን ለመጀመር ወደ ተግባር መግባቱ ተስፋ ሰጪ ጅማሮ እንደሆነ አንስተዋል።
በፍጥነት የምክክር ሂደቱ ሊጀመር እንደሚገባ አንስተው÷ ሂደቱ ውጤታማ መሆን ለችግሮች በዘላቂነት መፈታትና በተለይ በትግራይ የሚታዩ ውጥረቶች ተባብሰው ዳግም ወደ ጦርነት እንዳይገባ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡
በክልሉ ያለውን አውድ የሚያንጸባርቅ የምክክር ሥነ ዘዴ ተቀርጾ ሁሉንም ወገን አካታችና አሳታፊ የሆነ ምክክር እንዲካሄድ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚያስፈልግ እንዲሁም ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዎች በስፋት መከናወን እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ የወሰዳቸውን ግብዓቶች በመጠቀም በክልሉ የሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር ባጠረ ጊዜ እንዲጀመርና ሁሉንም አካታችና አሳታፊ እንዲሆን ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ኮሚሽነሮች መግለፃቸውን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!