ጉዳት የደረሰበትን የጊደብ ወንዝ ድልድይ በፍጥነት ወደ አገልግሎት ለመመለስ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጉዳት የደረሰበትን የጊደብ ወንዝ ድልድይ በፍጥነት ወደ አገልግሎት ለመመለስ እየተሰራ ነው አለ።
ከደብረማርቆስ ወደ ባሕር ዳር በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው የጊደብ ወንዝ ድልድይ ትናንት ሌሊት በጣለው ከባድ ዝናብ ባጋጠመው ጎርፍ ጉዳት ደርሶበታል።
በመንገዶች አስተዳደር የደብረማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ምህንድስና ኦፕሬሽን ቡድን መሪ መንግስቱ አስረስ በጎርፍ አደጋ የደረሰው ጉዳት ከደብረማርቆስ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደውን መንገድ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንዲስተጓጎል ማድረጉን ተናግረዋል።
ዲስትሪክቱ ተገጣጣሚ ድልድይ በፍጥነት በመገንባት የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አስረድተዋል።
በበላይነህ ዘለዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!