ማንቸስተር ሲቲ ዎልቭስን 4 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ከሜዳው ውጪ የተጫወተው ማንቸስተር ሲቲ ዎልቭስን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በተደረገው ጨዋታ ሃላንድ ሁለት ግቦችን ሲስቆጥር ሬይንደርስ እና ቼርኪ ቀሪ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡
ትናንት በጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል ቦርንማውዝን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በዛሬው ዕለት በተካሄዱ ጨዋታዎች ደግሞ ቶተንሃም በርንሌይን፣ ሰንደርላንድ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት አሸንፈዋል፡፡
አስቶን ቪላ እና ኒውካስል ዩናይትድ ያለምንም ግብ አቻ ሲለያዩ፤ ብራይተን እና ፉልሃም 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።