Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ታዳሽ ሃይልን በማልማት ምስራቅ አፍሪካን በኤሌክትሪክ ለማስተሳሰር እየሰራች ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ያላትን ዕምቅ ሃብት በማልማት ምስራቅ አፍሪካን በኤሌክትሪክ ለማስተሳሰር እየሰራች ነው አሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ፡፡

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኤሌክትሪክ በማስተሳሰር የአፍሪካ የሃይል ቋት ለመሆን ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት ያላትን የተፈጥሮ ሃብት ጥቅም ላይ እያዋለች ትገኛለች ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሃይል አቅርቦት እያከናወነቻቸው ያሉ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ከቀጣናው ባለፈ ሌሎች ሀገራትን ተጠቃሚ ለማድረግ ያችላሉም ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ዕምቅ የውሃ፣ የንፋስና የፀሐይ ተፈጥሮ ሃብቶች የኤሌክትሪክ ሃይል ለማልማት፣ ለማመንጨትና ለማሰራጨት ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥሩ አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ለማሳደግ ያከናወነቻቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

እየተካሄዱ ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ኃይል በማገናኘት ቀዳሚውን ስፍራ እንድትይዝ ያደርጋታል ብለዋል።

የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ እየተከናወኑ የሚገኙ የታዳሽ ኃይል ልማት ሥራዎች ከራሷ አልፎ ጎረቤት ሀገራትን ለማስተሳሰር የጀመረችውን ጥረት እንደሚያፋጥኑ መጥቀሳቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.