Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን አሜሪካና አካባቢው የተጀመረው የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ…

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጉዳዮች ለዘመናት ባለመግባባታችን ከታናናሾቻችን በታች ሆነናል አሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)፡፡
ኮሚሽኑ በሰሜን አሜሪካና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ያዘጋጀው መድረክ በዋሽንግተን ዲሲ ተጀምሯል፡፡
መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ አሜሪካ በእድሜ ከኢትዮጵያ ያነሰች ብትሆንም በዴሞክራሲ ትግበራ ግን ቁንጮ ላይ ደርሳለች፡፡
ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገሩ ግጭቶችና አለመግባባቶችን ስታሳልፍ በመቆየቷ እዚህ ደረጃ መድረስ አለመቻሏን አስረድተዋል፡፡
አሁን ግን የማንግባባቸውን እጅግ መሰረታዊ ምክንያቶች በሕዝባዊ ውይይት በመለየት ወደ ዘላቂ ሰላም ለመሸጋገር በጉዞ ላይ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ቅደመ ሁኔታና ልዩነት እየተሳተፉበት የሚገኝ ታሪካዊ ሒደት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ ምክንያቶች ቢሰደዱም የሀገራቸው ጉዳይ ያገባቸዋል በሚል በተለያዩ አማራጮች በምክክሩ ሒደት ለማሳተፍ ኮሚሽኑ አበክሮ እየሰራ ነው፡፡
አንዳንዶች ይህንን የኮሚሽኑን እንቅስቃሴ ለመግታት ቢንቀሳቀሱም ብዙዎች ግን ከኮሚሽ ጎን በመሆናቸው ሒደቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ነው፤ ለዚህም በአሜሪካ እየተካሄደ ያለው መድረክ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በዴሞክራሲ ቁንጮ ላይ በምትገኝ ሀገር እየኖሩ መርህ አልባ የሆነ ተቃውሞ የሚጠበቅ አይደለም ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ÷ ሒደቱን መደገፍ ባይቻል በዴሞክራሲያዊ መንገድ መጓዝ ግን የተሻለው ነው ሲሉ አጽንት ሰጥተዋል፡፡
በሒደቱ የቀሩ ሥራዎች ጥቂት ቢሆኑም እጅግ መሰረታዊ የሚባሉ ናቸው ማለታቸውንም ኮሚሽኑ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.