Fana: At a Speed of Life!

ዘላቂ የልማት ፍኖተ ካርታውን ለማሳካት አስቻይ ሁኔታዎችን ማሳደግ ከአመራሩ ይጠበቃል – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘላቂ የልማት ፍኖተ ካርታውን ለማሳካት አስቻይ ሁኔታዎችን ማሳደግ ከአመራሩ ይጠበቃል አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፡፡

የክልሉ የ25 ዓመታት አሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት ፍኖተ ካርታ እና የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና የማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ነው።

አቶ አረጋ ከበደ በመድረኩ እንዳሉት÷ ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ የሚተገበረው የ5 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅድ በሁሉም ዘርፎች እምርታዊ ለውጥ ማምጣት ያስችላል።

የሚፈለገውን ውጤት እውን ለማድረግ ሰላምን በዘላቂነት የሚያስጠብቅ እና የሕዝባችንን ጥያቄ የሚመልስ አመራር መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ከድህነት ለመውጣትና የሚፈለገውን ሁለንተናዊ እድገት ለማስመዝገብ ራዕይን መሸከምና ማሳካት የሚችሉ ተቋማትን መገንባት ይገባል ነው ያሉት።

አመራሩ ለእቅዱ እውን መሆን ራሱን የሚያዘጋጅ ከሆነ ለችግሮች ሳይበገር የ25 ዓመታት አሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት ፍኖተ ካርታና የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድን ማሳካት እንደሚችል ገልፀዋል፡፡

አስቻይ ሁኔታዎችን መጨመር እና ተጋላጭነትን መቀነስ ከሁሉም አመራር እንደሚጠበቅም አስገንዝበዋል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.