Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የፅናት ሽልማት ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የፅናት ሽልማት ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡

ፕሬዚዳንቱ የግድቡን መመረቅ ተከትሎ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት÷ ግድቡ የኢትዮጵያውያን የላብ፣ የደም እና የእንባ ውጤት ነው ብለዋል።

ያለፉት እና አሁን ያሉት መሪዎች ግድቡ እውን እንዲሆን ለሰነቁት ራዕይ እና ላሳዩት ድፍረት እናመስግናን በማለት ገልጸዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የፅናት ሽልማት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ ግድቡ የዓባይ ልጆችን ከብዙ በረከት ጋር የሚያስተሳስር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ግድቡ ዘላቂ የዕድገት ብርሃንን ይዞ እንዲመጣም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.