የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ምርቃት የተሰማትን ደስታ ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያውያን ኅብረት ምሳሌ በሆነው ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ የተሰማትን ደስታ ገልጻለች፡፡
የቤተክርስቲያኗ የጳጳሳት ጉባኤ ባስተላለፈው የደስታ መግለጫ መልዕክት፥ ለምረቃ የበቃው ግድብ ለመላው ኢትዮጵያውያን ብሎም አፍሪካውያን የስኬት ምሳሌ ነው ብሏል፡፡
ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እና የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ወደጉባ በማቅናት ከሀይማኖት አባቶች ጋር በህብረት በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ መገኘታቸውንም ቤተ ክርስቲያኗ አስታውቃለች፡፡