Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ደስታውን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ግንባታው ተጠናቆ ትናንት በተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ስኬት የተሰማውን ደስታ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የህዳሴ ግድቡን መጠናቀቅ አስመልክተው የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫው የወንጌላውያን ህብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻዲቁ አብዶ እንዳሉት፤ ከዘፍጥረት ጀምሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱ አራት ወንዞች አንዱ የሆነው ዓባይ ታሪካዊ ወንዝ ነው።

በዚህ ወንዝ ላይ በኢትዮጵያውያን የጋራ ጥረት የተገነባው የህዳሴ ግድብ በመጠናቀቁ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን በተመለከተ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብሁሃን የሚተላለፉ የሀሰት ትርክቶችን በመመከት ረገድ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንደወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጄ ጀንበሩ (ዶ/ር)÷ አዲሱን ዓመት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃትን እና የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት 50ኛ አመት በማስመልከት የምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል ብለዋል።

መርሐ ግብሩ መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም በመስቀል አደባባ እንደሚካሄድ ጠቁመው÷ በመርሐ ግብሩ መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እንዲገኙ በመግለጽ መልዕክት አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.