የሕዳሴ ግድብ መመረቅን ተከትሎ ነገ ለሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ የዋዜማ ትርዒት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ ለምረቃ መብቃቱን አስመልክቶ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ የዋዜማ የማርቺንግ ባንድ የሙዚቃ ትርዒት ተካሂዷል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እንዳስታወቀው÷ የግድቡን መመረቅ በማስመልከት በነገው ዕለት ለሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ቅድመ የጸጥታ ስራ ልምምድ እና የማርቺንግ ባንድ የሙዚቃ ትርዒት ተደርጓል።
የየተቋማቱ የማርቺንግ ባንድ አባላት በከተማው በተመረጡ 12 ቦታዎች ላይ በመዘዋወር ልዩ ልዩ ሀገራዊ ጣዕመ ዜማዎችን በማሰማት ትርዒት አቅርበዋል።
ከጸጥታ ቅድመ ጥንቃቄ ልምምድ ባሻገር የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ የማርቺንግ ባንድ አባላት የጋራ የአደባባይ ላይ የሙዚቃ ትርኢት አቅርበዋል።