Fana: At a Speed of Life!

በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 2ኛውን ከፍተኛ ውጤት ያመጣችው ተማሪ … ሃይማኖት ዮሃንስ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የብስራተ ገብርኤል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዋ ሃይማኖት ዮሃንስ በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 579 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2ኛውን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በመዲናዋ በተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች ሃይማኖት ዮሃንስ 579 በማምጣት ቀዳሚ ሆናለች፡፡

በዚህም ሃይማኖት ዮሃንስ በሀገር አቀፍ ደረጃ 2ኛውን ከፍተኛ ውጤት ያዝመዘገበች ሲሆን÷ ሌላኛዋ ተማሪ ሲምቦ ደረጀ ደግሞ በማህበራዊ ሳይንስ 548 ማስመዝገቧን ቢሮው ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

የብስራተ ገብርኤል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ዘላለም ደምሴ እንዳሉት÷ ተማሪ ሃይማኖት ዮሃንስ በጣም ጎበዝ እና በየዓመቱ 99 ነጥብ 9 ውጤት በማምጣት ተሸላሚ ናት፡፡

ተማሪዋ ትምህርቷን እንዲሁም አስተማሪዎቿን በሚገባ የምትከታተልና የጥሩ ሥነ ምግባር ባለቤት መሆኗንም አስረድተዋል፡፡

በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ 2ኛውን ከፍተኛ ውጤት በማምጣቷ መደሰታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ሺህ 384 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ያመጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም 888 የሚሆኑት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተማሪዎች ናቸው።

በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 8 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ከ50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት ያለፉት፡፡

50 ት/ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ ሲሆን ÷ 1 ሺህ 249 ት/ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.