Fana: At a Speed of Life!

ግዮንን የሚሸኙት ሳይሆን አብረው የሚኖሩት የሆነበት የሕዳሴ ግድብ 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ግዮንን የሚሸኙት ሳይሆን አብረው የሚኖሩት እንዲሆን ማድረግ ተችሏል አሉ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፡፡

የጎንደር ከተማ ህዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የተሰማውን ደስታ በሰላማዊ ሰልፍ ገልጿል።

በህዝባዊ ሰልፉ ላይ አቶ ቻላቸው ዳኘው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሕዳሴ ግድቡ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የጎንደር ከተማ የተጠናከረ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

ከዘመናት ቁጭት በኋላ በዚህ ዘመን ትውልድ በዓባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለስኬት መብቃቱ ኢትዮጵያዊውን በጋራ ከቆሙ ማሳካት የማይችሉት ነገር እንደሌለ ጉልህ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በብዙ ፈተናዎች አልፈን ችለን አሳይተናል ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው÷ ግድቡን ለመጨረስ የተከፈለው መስዕዋትነት ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

የሕዳሴ ግድብን ለማቋረጥ ምርጫ የቀረበለት የለውጡ መንግስት በኢትዮጵያ ጥቅም አልደራደርም በማለትና በመፅናት ግድቡን ማጠናቀቅ መቻሉን አንስተዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)  አመራር ሰጭነት ታላቁ ግዮን ወንዝ የሚሸኙት ሳይሆን አብረው የሚባጁበት፣ አብረው የሚኖሩት እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.