በክልሉ የወባ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች እየተተገበሩ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወባ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን እየተገበርኩ ነው አለ የክልሉ ጤና ቢሮ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ በክልሉ ለወባ መራቢያ ምቹ ሁኔታ ያለባቸውን አካባቢዎች በቅኝት እና ምላሽ ሥርዓት በመለየት ጫናውን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በዚህ መሰረትም የወቅቱን ዝናብ ተከትሎ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና ማዳፈን ተግባራት ሕብረተሰቡን በማስተባበር እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በቀጣይ ትምህርት ቤቶችን፣ ሃይማኖት ተቋሟትን እና የሕዝብ አደረጃጀቶችን በማስተባበር እንደሚሰራም ነው የስረዱት፡፡
የወባ በሽታን ለመከላከል በክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ የወባ ጫና ባለባቸው ሦስት ዞኖች እና ሁለት ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ 425 ሺህ 827 ነዋሪዎች የሚያገለግሉ 212 ሺህ 914 የአጎበር ሥርጭት መካሄዱን ተናግረዋል።
በዚህም ውጤታማ የአጎበር አጠቃቀም እንዲኖር የቅኝት እና ምላሽ ሥርዓት መዘርጋቱን አቶ ሳሙኤል አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ 13 ወረዳዎች የጸረ ወባ ኬሚካል ርጭት 875 ሺህ 414 የቤተሰብ አባላት ተጠቃሚ ለማድረግ የባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል ነው ያሉት፡፡
የበሽታውን ሥርጭት ለመከላከል በየደረጃው ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው ÷ በቀጣይ ሦስት ወራት የምርመራና ሕክምና ሥራዎች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የወባ በሽታ ጫናውን ችግር በማይሆን ደረጃ ለመቀነስ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!