“ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ 45ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
የውይይት መድረኩ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ሆረ ፊንፊኔ እና ሆረ ሀርሰዲ ቢሾፍቱ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየመከረ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ጀሚላ ሲምቢሩ እና የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛን ጨምሮ ምሁራን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በበዓሉ ላይ ትኩረቱን ባደረገው በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እየተካሄደባቸው ይገኛል።
ጉሚ በለል በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አዘጋጅነት በየወሩ በተለያዩ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ ነው፡፡
በመራኦል ከድር
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!