Fana: At a Speed of Life!

የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ‘ሄቦ’ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ‘ሄቦ’ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የም ዞን ሳጃ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በድምቀት እየተከበረ በሚገኘው በዓል ላይ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና በክልሉ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች ተገኝተዋል፡፡

ሄቦ ከጭጋግና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ምዕራፍ መሸጋገሪያ በዓል መሆኑ ተገልጿል።

የሄቦ በዓል የአዲስ ዓመት ብርሃን ማብሰሪያ፣ በተለያየ ምክንያት ከአካባቢው ርቀው የሚኖሩ ከቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር የሚገናኙበት፣ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ታላቅ በዓል እንደሆነ ተነግሯል።

በወርቅአፈራው ያለው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.