አርቲስት ፍሬህይወት ባህሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርቲስትና ኮሜዲያን ፍሬሕይወት ባህሩ ባጋጠማት ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡
አርቲስቷ የቀለጠው መንደር፣ ፎርፌ፣ ረመጥ፣ ነቃሽ እና ሌሎች በርካታ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተሰሩ ቴአትሮች ላይ ተውናለች ።
አርቲስት ፍሬህይወት በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በውዝዋዜ እና ዳንስ ተቀጥረው ችሎታቸውን በመድረክ ካሳዩት ከያኒያን መካከል አንዷ ነበረች።
በሀገር ፍቅር ቴአትር ለበርካታ ዓመታት በሙያዋ ያገለገለችው አርቲስቷ፤ በበርካታ ፊልሞች፣ የቴሌቪዥን ድራማ እና የሙዚቃ ክሊፖች ላይ በትወና መሳተፏን የሀገር ፍቅር ቴአትር መረጃ አመልክቷል።