Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ልማት ፎረም መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ካፒታል ፎረም 2025 በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በኢትዮጵያ መንግስት እና በዓለም ባንክ በጋራ የተዘጋጀው ፎረሙ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የዓለም ባንክ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ፎረሙ ክህሎትን መገንባት፣ የስራ ዕድል ፈጠራን እንዲሁም ልማት እና እድገትን ማፋጠን በሚሉ ሀሳቦች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚመክር ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያን ሰብዓዊ ካፒታል ለማሳደግ የሚያስችሉ የመንግስት አመራሮችን፣ ፖሊሲ አውጭዎችን፣ ባለሙያዎችን እና ዓለም አቀፋዊ አጋሮችን በአንድ ማስባሰብ የፎረሙ አላማ ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.