የኢሬቻ ፎረም እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢሬቻ ፎረም በቢሾፍቱ ከተማ በገልመ ሀርሰዴ እየተካሄደ ነው።
በፎረሙ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
እንዲሁም አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በፎረሙ ላይ ተሳትፈዋል።