ኢሬቻ አብሮነትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ አለው – አቶ ኃይሉ አዱኛ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ የምስጋና እና የእርቅ በዓል የሆነው የኢሬቻ በዓል አብሮነትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ አለው አሉ።
አቶ ኃይሉ አዱኛ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ባዘጋጀውን የኢሬቻ ኮንሰርት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ የኦሮሞ ህዝብ የፈጣሪ እና የፍጥረትን ግንኙነት የሚበይንበት ፍልስፍና አለው።
የኦሮሞ ህዝብ የሚመራበት የገዳ ስርዓት እንዳለው ገልጸው፤ የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርዓት ነጸብራቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢሬቻ ፈጣሪ ላደረገው ሁሉ የሚመሰገንበት እና ለሚቀጥለው ደግሞ ተስፋ የሚሰነቅበት ዘርፈ ብዙ እሴቶች ያሉት በዓል ነው ብለዋል።
የኦሮሞ ህዝብ ያለ ምንም የፖለቲካ፣ ኃይማኖት እና ጎሳ ልዩነት አብሮ ደምቆ የሚታይበት የኢሬቻ በዓል አብሮነት እና አንድነትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
ከኦሮሞ ህዝብ ባሻገር ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ተሳትፎ በማድረግ ወንድማማችነታቸውን የሚያሳዩበት በዓል መሆኑን ገልጸው፤ መከባበር እና መተሳሰብ የሚታይበት መድረክ እንደሆነ ተናግረዋል።
ወንድማማችነትን የሚያጠናክረው የኢሬቻ በዓል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደመቀ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ለዚህም ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንን ጨምሮ መገናኛ ብዙሃን የጎላ ሚና ማበርከታቸውን አስረድተዋል።
ኢትዮጵያን ለማብሰር እየሰራ ለሚገኘው ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ኢሬቻን ጨምሮ ለባህላዊ እሴቶት ትኩረት በመስጠት ለሚሰራው ስራ በኦሮሚያ ክልል መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!