Fana: At a Speed of Life!

የሠንደቅ ዓላማ ቀን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር፣ ክብር እና ቃል ኪዳን የሚያድስበት ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሠንደቅ ዓላማ ቀን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር፣ ክብር እና ቃል ኪዳን በልቡ የሚያድስበት ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።

18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ መርሐ ግብሮች ተከብሯል።

ፕሬዚዳንት ታዬ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የሠንደቅ ዓላማ ቀን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር፣ ክብር እና ቃል ኪዳን በልቡ የሚያድስበት፣ የጋራ ማንነታችንን የምናጎለብትበት እና የነገ ተስፋችንን የምናጸናበት ታላቅ ብሔራዊ ዕለት ነው።

ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ያጋጠሟትን ከባድ የህልውና ፈተናዎች በሕዝቦቿ የአንድነት ክንድ በጽናት ተሻግራ ዛሬ የራሷን ዕድል የመወሰን ብቃቷን እያስመሰከረች ትገኛለች ያሉት ፕሬዚደንቱ÷ ይህም በምኞት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በስኬቶች የተደገፈ መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በቢሊየኖች የሚቆጠር ችግኞችን በመትከል በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ከፊት ሆና የመምራት ሚና ማረጋገጥ መቻሏን ጠቅሰው÷ የግብርና ምርታችንን በማሳደግ ረገድም ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በፍጥነት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።

የተፈጥሮ ጋዝ ኃብታችንን ለኢንዱስትሪ ግብዓት እና ለኃይል ማመንጫነት ማዋላችን የእድገት እና የብልጽግና ጉዞን ያፋጥናል ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ ይህ ሁሉ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ብሔራዊ አንድነታችን ሲጠናከር እና ሰላማችን አስተማማኝ ሲሆን ነው ብለዋል።

በቀጣናው የጋራ ተጠቃሚነት እና ፍትሃዊ የባሕር በር የመጠቀም እና የማግኘት መብታችንን በሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ እንዲሁም በሰጥቶ መቀበል መንገድ ማስከበራችን ይቀጥላልም ነው ያሉት።

ሠንደቅ ዓላማው በላባችን እና በዕውቀታችን ሀገራችንን ወደ ከፍታ ለማውጣት ለእያንዳንዳችን ኃላፊነት ይሰጠናል በማለት ሁሉም ዜጋ የኢትዮጵያን የእድገት ግስጋሴ ለማሳካት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.