በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 5 የትምህርት ኢኒሼቲቮች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚረዱ አምስት አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ይፋ አድርጓል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ዘርፍ ጉባዔ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የትምህርት ሚኒስትር ዴዔታ አየለች እሸቴ እና የክልሉ አፈ ጉባኤ ፋጤ ሴርሞሎን ጨምሮ የፌደራልና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድርና የትምርት ቢሮ ሃላፊ አንተነህ ፈቃዱ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማሳደግ ዘርፍ ብዙ ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡
በዚህ መሰረትም ደረጃቸውን የጠበቁ ት/ቤቶችን ከመገንባት ጀምሮ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን መተግበር እንደተጀመረ አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩል 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሃብት በማሰባሰብ የትምህር ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ተችሏል ነው ያሉት፡፡
የመምህራንን ብቃት የማሳደግ ሥራ መከናወኑን ጠቁመው ÷ 417 ሺህ የመማሪያ መጽሐፍት ታትመው ለት/ቤቶች መሰራጨታቸውንም ተናግረዋል፡፡
በጥላሁን ይልማ