ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሠንደቅ አላማ ቀንን አከበረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን 18ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አክብሯል።
በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አመራሮች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡
የሠንደቅ ዓላማ ቀን ‘ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ’ በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
ሠንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር መንግሥትና ሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ሥልጣን፣ ነፃነት፣ ዕድገትና ማሕበረሰባዊ ትስስር መፍጠሪያ መሣሪያ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ የታተመ የሀገራዊ አንድነትና ነፃነት መገለጫ ታላቅ የብሔራዊ ኩራት አርማ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
በሶስና አለማየሁ