Fana: At a Speed of Life!

2ኛው የአፍሪካ የክህሎት ሳምንት መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 2ኛው የአፍሪካ የክህሎት ሳምንት “የአፍሪካን የኢንዱስትሪ አቅም ማጎልበት፣ ለፈጠራ፣ ለእድገት እና ለዘላቂነት ክህሎት ልማት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ነው።
የክህሎት ሳምንቱ የክህሎት እና የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲዎች፣ የክህሎት ልማት ጥራት እና አካታችነት፣ የኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት፣ ሀብት መጋራት፣ ተቋማዊ ልማት፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው በዚህ መድረክ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍን ጨምሮ የሀገራት ተወካዮች፣ አምባሳደሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በክህሎት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት የአፍሪካ የልማት አጀንዳዎች እንዲሳኩ ከማድረግ በተጨማሪ የዓለም እድገትን የሚገነባ ቁልፍ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሚኒስቴሩ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት እንዲስፋፋ የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን ቀርጾ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው÷ ስራ ፈላጊዎች ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ የሚያስችል ጥራት ያለው የክህሎት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም የሰለጠኑ ወጣቶች በተለያዩ የኢንዲስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.