Fana: At a Speed of Life!

15ኛው የኢትዮጵያ ኢቫሉዌሽን አሶሴሽን ዓመታዊ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 15ኛው የኢትዮጵያ ኢቫሉዌሽን አሶሴሽን ዓመታዊ ጉባኤ “ሀገራዊ የእቅድና ምዘናን አቅም ማሳደግ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ይገኛል።
ጉባኤውን የኢትዮጵያ ኢቫሉዌሽን አሶሴሽን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኒሴፍ ጋር በትብብር ያዘጋጁት ሲሆን÷ ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማትና ከአራት ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ከ150 በላይ ተሳታፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ በሚኒስቴሩ የተዘጋጀ የእቅድ፣ ክትትል እና ግምገማ ምዘና ፖሊሲ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ ሚኒስቴሩ የክትትልና ግምገማ ስርዓትን ለመገንባት እና ዲጂታላይዝ ለማድረግ፣ ጥራት ያለውን መረጃ ለማመንጨት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ማንኛውም የልማት ግብና ሀገራዊ ግንባታ የሚጀመረው ከእቅድ መሆኑን አንስተው÷ ዩኒቨርሲቲውም የሰው ኃይልን በማሰልጠን የተለያዩ ምርምሮችን በማካሄድ ከእቅድና ግምገማ ከተቋማት ጋር እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢቫሉዌሽን አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ደረጀ ማሞ ማሕበሩ በመንግሥት ተቋማት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት በአቅም ግንባታ ላይ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
በበሪሳ ኃ/ማርያም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.