የምሥራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መቆጣጠሪያ ድርጅት የሚኒስትሮች ም/ቤት ስብሰባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መቆጣጠሪያ ድርጅት የሚኒስትሮች ምክር ቤት 70ኛ ዓመታዊ ስብሰባ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
መድረኩ በኢትዮጵያ አስተጋጅነት “አስተማማኝ ድንበር ዘለል የሰብል ተባዮች መከላከል ሥራ ለቀጣናዊ ምግብ ዋስትና መረጋገጥ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የአባል ሀገራት ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ የሚገኘው።
በፈረንጆቹ 1962 በአዲስ አበባ በተፈረመ ዓለም አቀፍ ስምምነት በምስራቅ አፍሪካ ተባይን ለመከላከል የተመሰረተው ድርጅቱ ÷ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኝ ሀገራትን በአባልነት ይዟል።
ድርጅቱ የበረሃ አንበጣ የሚያደርሰውን ጉዳት መከላከያና መቆጣጠሪያ መንገዶችን ለመተንበይ የተቋቋመ ሲሆን÷ አሁን ላይ ከበረሃ አንበጣ ባሻገር ሌሎች ድንበር ዘለል ተባዮች መከላከልንም በኃላፊነቱ ውስጥ አካትቶ እየሰራ ይገኛል።
የድርጅቱ አባል የሆኑት ኢትዮጵያ፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ተወካዮቻቸው በተገኙበት 69ኛው የድርጅቱ ዓመታዊ ስብሰባ በኬንያ ሞምባሳ መካሄዱ ተገልጿል።
ድርጅቱ የተለያዩ ዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም የተለያዩ የቁጥጥር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል።
የበረሃ አንበጣ ሥርጭትን ለመቆጣጠር ከተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መንገዶችን በመጠቀም እየተሰራ መሆኑም በስብሰባው ተጠቅሷል፡፡
በአድማሱ አራጋውፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!