ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ዛሬ ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው የሊጉ ጨዋታ ከእረፍት በፊት ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን እና መደበኛ የጨዋታ ሰዓት ተጠናቅቆ በተጨመረ ደቂቃ መላኩ አሰፋ ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ሲዳማ ቡና አሸናፊ ሆኗል።
የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ ነገሌ አርሲ ከባሕር ዳር ከተማ ቀን 10 ሰዓት እንዲሁም 12 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ እና ምድረ ገነት ሽረ ይገናኛሉ።
ቀደም ስል ቀን 7 ሰዓት ላይ በተካሄደው የሊጉ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!