የፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 ውድድር በመጪው ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ700 በላይ የቅድመ ማጣሪያ ተፎካካሪዎች መካከል የተለዩ 16 ከዋክብትን ይዞ የጀመረው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 ውድድር በመጪቅ ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል።
በዕለቱ የምድብ ሁለት ስምንት ተወዳዳሪዎች ከዛየን ባንድ ጋር ስራዎቻቸውን በሁለት ዙር ያቀርባሉ።
ለ13 ሳምንታት በሚዘልቀው በዚህ ምዕራፍ ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ሳምንታት በራሳቸው፣ በዳኞች እና በተመልካቾች የሙዚቃ ምርጫ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
የሙዚቃ ባለሙያዎች እና ተመልካቾች በአጭር የጽሑፍ መልዕክት በሚሰጡት ድምጽ ተወዳዳሪዎቹ የሚዳኙ ይሆናል።
በምዕራፉ ለፍፃሜ ለሚደርሱ አራት ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፤ ለፋና ላምሮት 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ያልፋሉ።
የምዕራፍ 21 ውድድር በመጪው ቅዳሜ ከ6:00 ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት በፋና ቴሌቪዥን፣ በፋና+፣ በፋና ፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾች እንዲሁም በ www.fanamc.com ይከታተሉ።
በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የተወዳዳሪዎችን ኮድ በመላክ እየተዝናኑ ድምጽ በመስጠት የዳኝነቱ አካል ይሁኑ።
በለምለም ዮሐንስ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!