Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የመደመር መንግሥት ምስረታ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የምክር ቤቱን 7ኛ የሥራ ዘመን የመመስረቻ ጉባዔ በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በዚህ ወቅትም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተመረጡ አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የምክር ቤቱ ተመራጭ አባላትም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.