ኢትዮጵያ ቡና በአዳማ ከተማ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአዳማ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ነቢል ኑሪ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናው በፍቃዱ ዓለማየሁ 73ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡