የአውሮፓ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡
በዚህም መሠረት በምድብ አንድ ጣሊያን ከ ሰሜን አየርላንድ እንዲሁም ዌልስ ከ ቦስኒያ ተደልድለዋል።
በምድብ ሁለት ዩክሬን ከስዊድን እንዲሁም ፖላንድ ከአልባኒያ ተገናኝተዋል።
በምድብ ሦስት ቱርክ ከ ሮማኒያ እንዲሁም ስሎቫኪያ ከኮሶቮ ሲገናኙ በምድብ አራት ዴንማርክ ከሰሜን ሜቄዶንያ እንዲሁም ቼክ ሪፐብሊክ ከሪፐብሊክ አየርላንድ መደልደላቸው ተመላክቷል፡፡
16 የአውሮፓ ሀገራት ተካፋይ በሚሆኑበት የ2026 ዓለም ዋንጫ 12ቱ ተሳታፊ ሀገራት ቀድመው የታወቁ ሲሆን÷ ቀሪ አራቱ ሀገራት በቀጣይ የሚታወቁ ይሆናል፡፡
በዳዊት መሐሪ