በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈርሟል፡፡
ስምምነቱን የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር አረጋ ከበደ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን በመወከል ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ተፈራርመዋል።
በአፍሪካ ህብረት እና በኢጋድ አደራዳሪነት ወይይት እና ድርድር ሲካሄድ መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን፥ በዚሁ መሰረት የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈርሟል፡፡
ርዕሰ መሰተዳድሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ ዛሬ ለክልላችን ህዝብ የመጀመሪያው ትልቅ የሰላም ኩነት የተካሄደበት ቀን ነው ብለዋል።
ከግጭት አሸናፊም ተሸናፊም የለም፥ ከሰላም ሁሉም ያተርፋል፥ ስምምነቱ ለሰላም ወዳድ ህዝባችን ትልቅ እፎይታን ይሰጣል ነው ያሉት፡፡
የህዝብና የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለመጡ ወንድሞቻችን እንደ መንግስት አድናቆትና ክብር አለኝ ብለዋል፡፡
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ባደረጉት ንግግር፥ ማንኛውም ግጭት መጨረሻው ውይይትና ድርድር ነው ብለዋል።
ችግሮችና የሀሳብ ልዩነትን በንግግር መፍታት ፖለቲካዊ ሽንፈት ሳይሆን ጥበብና ብልጠት መሆኑን ገልጸው፥ ችግሮችን ለመፍታት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበር ተገቢ አለመሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ አዳዲ በበኩላቸው፥ ስምምነቱ የሀገሪቱን ቀጣይ መዳረሻ የሚያቃና ነው ብለዋል።
በበላይ ተስፋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!