ለነዋሪዎቹ የጋራ መገልገያ መሰረተ ልማቶች መሟላታቸውን ተመልክተናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የፒያሳ ነዋሪዎች በገቡበት መንደር የጋራ መገልገያ መሰረተ ልማቶች መሟላታቸውን ተመልክተናል አሉ፡፡
ከንቲባዋ በዛሬው ዕለት በበንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በመገኘት የፒያሳ ነዋሪዎችን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡
ልጆች ምቹ መጫወቻ ሜዳዎች፣ ወጣቶች የስፖርት ሜዳና ለነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠሩ ሱቆች እንዲሁም የጋራ መገልገያ መሰረተ ልማቶች ተሟልተውላቸው በማየታችን በጣም ደስ ብሎናል ነው ያሉት።