Fana: At a Speed of Life!

ለዘላቂ የአምራች ኢንዱስትሪ ዕድገት የተሰጠው ትኩረት ውጤት እያመጣ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪና የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ ለዘላቂ የአምራች ኢንዱስትሪ ዕድገት አስቻይ ሁኔታዎችን በመፍጠርና ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል አሉ።

የመደመር መንግሥት ለኢንዱስትሪያዊነት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠርና በቅንጅት በመሥራት ዘላቂና ውጤታማ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ዕድገት ማምጣት ላይ ትኩረት አድርጓል።

የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል አባላት ዛሬ በባህር ዳር ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የብረታ ብረት፣ የጨርቃጨርቅ እና የአግሮ ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

‎አምባሳደር ግርማ ብሩ በወቅቱ እንዳሉት፤ መንግሥት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ነባራዊ ሁኔታ በመቃኘት እያጋጠሙ ለሚገኙ ችግሮች መፍትሔ እየሰጠ ይገኛል።

‎ካውንስሉ በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎችን በቅንጅት በመፍታት፣ ፋብሪካዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩና ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ጉብኝቱ ኢንዱስትሪዎቹን በመቃኘት እያጋጠሙ ለሚገኙ ችግሮች በቅንጅት መፍትሔ መስጠት መሆኑን ጠቅሰው፤ የባህርዳር ኢንዱስትሪዎች በተኪ ምርት እና ከግብርና ዘርፍ ጋር ጠንካራ ትስስር በመፍጠር ተጨባጭ ውጤት ማሳየታቸውን መመልከት ተችሏል ብለዋል።

ለዘላቂ የአምራች ኢንዱስትሪ ዕድገት አስቻይ ሁኔታዎችን ከመፍጠር ባለፈ ቅንጅታዊ አሠራር መጠናከሩ ለዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ካውንስሉ ከባለሀብቶች የሚቀርቡለትን መዋቅራዊ ችግሮች በመፍታት ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ የሚኖረውን ድርሻ ለማሳደግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

‎የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው፤ በዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

‎በዚህም ገቢ ምርቶችን የሚተኩ ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ ማደጋቸውን፣ ሰፊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን እና ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን አስረድተዋል።

‎ባህርዳር ለውጡን ተከትሎ በዘርፉ ትልቅ ስኬት እያሰመዘገበች መሆኗን ጠቅሰው፤ ካውንስሉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በባህር ዳር ከተማ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ ወደ ኢንዱስትራላይዜሽን በሚደረገው ጉዞ ላይ መሰረት የሚጥሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በካውንስሉ ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ መሻሻሎች መኖራቸውን መታዘብ መቻላቸውን ጠቁመዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በባህር ዳር ከተማ በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ከፍተኛ የስራ መነቃቃት መኖሩን ገልጸው፤ በአመራሩ እና በአምራቹ መካከል ያለው ቅንጅት ጠንካራ መሆኑን መመልከት ችለናል ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.