አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የመንግሥት ቢሮክራሲ መቀነስ እንዳለበት ያምናል ለዚህም በቁርጠኝነት ይሰራል አሉ።
አሁን አንድ ሰው አገልግሎት ለማግኘት በጣም በተራዘመ እና በገንዘብ በታገዘ መንገድ ለመሄድ ይገደዳል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር)፤ ይህን በቴክኖሎጂ መስበር እንደሚገባ ገልጸዋል።
ነገር ግን ይህንን ማድረግ ካልተቻለ የሚጠበቀው ለውጥ እንደማይመጣ ገልጸዋል፡፡
የተቋማት አመራሮች ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ለሀገር እድገት ማዋል እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በመሆኑም በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መንግሥት ቢሮክራሲን በመቀነስ አገልግሎትን ተደራሽ፣ ቀላልና ቀልጣፋ ማድረግ ይቻላል ነው ያሉት።