በኦሮሚያ ክልል የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን ዳቦ ሃና ወረዳ በዛሬው ዕለት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ እንዳሉት÷ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ሀገርና ትውልድን የማዳን ስራ ነው።
በክልሉ ለ60 ቀናት በሚቆየው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ 6 ሺህ 386 ተፋሰሶች እንደሚለሙ አስታውቀዋል።
በዚህም በተለያዩ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች 3 ሚሊየን 193 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚለማ ገልጸው÷ 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች እንደሚሳተፉም አመላክተዋል።
በአሊዳን መሃመድ