Fana: At a Speed of Life!

‘ሲቢኢ ኮኔክት’ የተሰኘ የውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያና መቀበያ መተግበሪያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘ሲቢኢ ኮኔክት’ የተሰኘ የውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያና መቀበያ መተግበሪያ ይፋ አድርጓል፡፡

ባንኩ ከስታር ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽንስ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት ያስጀመረው ዲጂታል ዋሌት የውጪ ሀገር የመገበያያ ገንዘቦችን ወደ ሀገር ቤት ለመላክ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በዶላር ገቢ በማድረግ በፈለጉበት ወቅት ወደፈለጉት ባንክና ዋሌት ሒሳብ መላክ የሚያስችል መሆኑም በይፋ ማድረጊያ መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

የባንኩ የኮርፖሬት አገልግሎቶች ኤክስኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ዲጂታል ዋሌቱ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን በማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ያለምንም ክፍያ የውጪ ሐዋላ መላክና መቀበል የሚችሉበት ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ መላላኪያ ሆኖ እንደሚያገለግል አመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም ዓለምአቀፍ የክፍያ ካርዶችንና ሕጋዊ የውጭ ገንዘብ አስተላላፊ ወኪሎችን መጠቀም የሚያስችል ሲሆን፥ ሕጋዊ የውጭ ምንዛሪ ገበያን እንዲከተሉ የሚያበረታታ ነው፡፡

 

ሲቢኢ ኮኔክት ዓለምአቀፍ ደረጃን ያሟላና ደኅንነቱ የተጠበቀ በመሆኑ ባንኩ በውጪ ምንዛሪ የሐዋላ አገልግሎት የዘርፉን የገበያ ድርሻ እንዲመራ ያስችለዋል ነው የተባለው፡፡

 

ሲቢኢ ኮኔክት ዓለምአቀፍ ደረጃን ያሟላና ደኅንነቱ የተጠበቀ በመሆኑ ባንኩ በውጪ ምንዛሪ የሐዋላ አገልግሎት የዘርፉን የገበያ ድርሻ እንዲመራ ያስችለዋል ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.