የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት አመራሮችና አባላት በመዲናዋ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራሮችና አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል ሲካሄድ የነበረው የድርድር ሒደት ተቋጭቶ በቅርቡ የሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወቃል።
በትናንትናው ዕለትም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በአፋሕድ መካከል የተደረሰውን ዘላቂ የሰላም ስምምነት ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል።
የአፋሕድ አመራርና አባላት በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በዚህም የዓድዋ ድል መታሰቢያን፣ በከተማዋ የተከናወነውን የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በፌቨን ቢሻው