አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 4 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ24ኛ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 4 ለ 0 በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት አጠናክሯል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኤላንድ ሮድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አርሰናል ማርቲን ዙቢሜንዲ እና የሊድሱ በረኛ ካርል ዳርሎ በራሱ ላይ ባስቆጥሯቸው ግቦች 2 ለ 0 እየመራ ወደ እረፍት አምርቷል፡፡
ከረፍት መልስ ቪክተር ዮኬሬሽ እና ጋብሬል ጀሱስ ባስቆጠሯቸው ግቦች አርሰናል 4 ለ 0 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ማጠናከር ችሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም አርሰናል ነጥቡን ወደ 53 ከፍ በማድረግ ከተከታዮቹ ማንቼስተር ሲቲ እና አስቶንቪላ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 7 አስፍቷል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ቦርንማውዝ ዎልቭስን 2 ለ 0 ሲያሸነፍ፤ ብራይተን እና ኤቨርተን 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡